Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርት ሥርዓቱን የሚያሳልጡ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀልጣፋ የትራንስፖርት ሥርዓት ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች በየካ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የየካ 2 የተሽከርካሪ ማቆሚያ መርቀው ሥራ አስጀመረዋል።

በዚሁ ወቅትም፤ ከለውጡ ወዲህ 35 ሺህ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚያስችሉ 150 የመኪና ማቆሚያዎች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የትራንስፖርት ሥርዓቱን የሚያሳልጡ የተሽከርካሪ፣ የብስክሌትና የእግረኛ መንገዶች በስፋት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተሽከርካሪ ማቆሚያዎቹና የመንገድ መሠረተ-ልማቶቹ የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ብለዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው የተሽከርካሪ ማቆሚያ በአንድ ጊዜ 1 ሺህ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.