Fana: At a Speed of Life!

ቤተክርስቲያኗ በመዲናዋ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ለሚገኙ የልማት ሥራዎች የምታደርገውን ሁሉን አቀፍ ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች አሉ ብፁዓን አባቶች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶች በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላ ብፁዓን አባቶች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ብፁዓን አባቶች በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በተለይም የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ውብና ጽዱ በማድረግ ለኑሮ ምቹ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ መዳረሻ እንድትሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኮሪደር ልማት ሥራው አስፈላጊውን ትብብር እንዳደረገች አጽንኦት መስጠታቸውንም የከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የኦንላይን ሚዲያ አስተዳደር ዳይሬክተር ብሩክሰው ይልማ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ቤተክርስቲያኗ በመዲናዋ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች የምታደርገውን ሁሉን አቀፍ ትብብርና እገዛ አጠናክራ እንደምትቀጥል ብፁዓን አባቶች አረጋግጠዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ÷ የአፍሪካ መዲና እና የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የዲፕሎማሲ መናገሻ የሆነችውን አዲስ አበባ ይበልጥ ለማልማት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በከተማዋ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ለምታደርገው ሁሉን አቀፍ ትብብርና ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.