Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ከ72 ሺህ በላይ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለፉት 11 ወራት 72 ሺህ 374 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ተካሂዷል።

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል እና የወሳኝ ኩነት ዘርፍ ኃላፊ ሰለሞን ደነቀ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ በበጀት ዓመት 73 ሺህ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ለማካሄድ ታቅዶ በ11 ወራት 72 ሺህ 374 ዜጎችን የመመዝገብ ሥራ ተከናውኗል።

በዚህም 56 ሺህ 239 የልደት፣ 2 ሺህ 913 የሞት፣ 10 ሺህ 781 የጋብቻ፣ 2 ሺህ 415 የፍቺ እና 26 የጉድፈቻ ምዝገባ ተካሂዷል ብለዋል።

በመደበኛነት በ930 ቀበሌዎች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው÷ 703 ቀበሌዎች በዲጂታል ሥርዓት የምዝገባ ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ከተለያዩ አገልግሎቶች ጋር የተቆራኘ በመሆኑ የተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነ ገልጸው÷ በሁሉም ቀበሌዎች ምዝገባውን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በጤና ተቋማት የሚከሰቱ የልደትና ሞት ኩነቶችን ባለሙያዎችን በመመደብ በ56 የጤና ተቋማት የማከናወን ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተው÷ በፍርድ ቤቶች ውሳኔ ያገኙ ፍቺ ፈፃሚዎች በፍርድ ቤቶች ምስክር ወረቀት እንዲሰጣቸው በመግባባት ምዝገባዎችን የማካሄድ ስራዎች መሰራታቸውንም ገልጸዋል።

ከትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር የትምህርት ቤቶች ምዝገባ በልደት ምስክር ወረቀት እንዲሆን ቅንጅታዊ ስራዎች መከናወናቸውንም አብራርተዋል።

በዚህም በተሰራው ስራ የተሻለ አፈፃጸም እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸው÷ ከተለያዩ ተቋማት ጋር እየተሰራ ያለው ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.