Fana: At a Speed of Life!

የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በማስቀጠል የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ይበልጥ በማስቀጠል የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን።

የክልሉ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እየተገመገመ ነው።

አቶ አሻድሊ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ በኩል አበረታች ውጤቶች የታዩበት ነው።

በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፎች የታቀዱ ሥራዎችን እስከታች በማውረድ ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

‎በአሶሳ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የሕዝቡን ጥያቄ የመለሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ይህም የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ከተማ ያደርጋታል ነው ያሉት።

‎በግብርና እና በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር የተከናወኑ ተግባራትም ሕዝቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ አቅርቦትን በማሻሻል ገበያ ማረጋጋት መቻሉን አንስተዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በአጠቃላይ በክልሉ የተከናወኑ አበረታች ተግባራትን በላቀ ጥረት በማስቀጠል በአዲሱ በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ርብርብ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

‎አመራሩ በተቀናጀ ሁኔታ የሕብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆን እንዳለበት ማሳሰባቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.