Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ለሚያከናውናቸው ሥራዎች ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን – የክልሉ ተወላጆች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል ተወላጆች የክልሉ መንግስት ለሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን አሉ፡፡

በነገው ዕለት በሚጀመረው የክልሉ 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ወደ ክልሉ የገቡ የሐረሪ ተወላጆች በክልሉ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በዓለም አቀፉ የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት፣ በከተማው የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶች እና የሕዝብ መናፈሻዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ተወላጆቹ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት÷ በሐረር ከተማ እና በከተማው በሚገኘው የዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከዛሬ ባለፈ ለነገው ትውልድ መሰረት የሚጥሉ ናቸው፡፡

የኮሪደር ልማቱ በከተማው ይስተዋል የነበረውን የፅዳት ጉድለት በማስቀረት ንፁህ፣ ውብና ምቹ የመኖሪያ አካባቢን መፍጠሩ አውስተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሐረርን ቀደምት ገናናነት የሚመልስ እንደሆነ መጥቀሳቸውን የክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

ጥንት አባቶች አንፀው ያቆዩትን ዓለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ የተሰራው የመልሶ ማልማት ስራም ቅርሱ ቀደም ሲል ከተደቀነበት አደጋ ከመታደግ ባለፈ አካባቢው ለጎብኚዎችና ለነዋሪዎች ምቹ ሆኖ በመመልከታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሥራው ትውልዱ ከታሪክ ተወቃሽነት ወደ ታሪክ ሰሪነት ያሸጋገረ መሆኑን ጠቁመው ÷ አመራሩ ከንግግር ባለፈ ህዝብና ተቋማትን በማስተባበር ያለምንም ተጨማሪ ወጪ ያከናወነው በተግባር የተገለፀ ውጤት ሁሌም ሲዘከር የሚኖር ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ለሚያከናውናቸው ሥራዎች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.