የይርጋለም ከተማን የኮሪደር ሥራ በፍጥነትና ጥራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የይርጋለም ከተማን የኮሪደር ልማት ሥራ በፍጥነትና በጥራት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር የተሰሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
አቶ ደስታ ሌዳሞ የይርጋለም ኮሪደር ሥራን በጎበኙበት ወቅት እንዳሉት÷ ከተማዋን ለኑሮ ምቹ፣ ጽዱ እና ደረጃዋን የጠበቀች እንድትሆን የተጀመረው ሥራ የሚበረታታ ነው፡፡
የኮሪደር ልማት ሥራውን በፍጥነትና ጥራት ገንብቶ ለማጠናቀቅ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመው÷ ሕብረተሰቡ እያደረገ ላለው ትብብር አመስግነዋል፡፡
ከኮሪደር ልማቱ ጋር በተያያዘ በከተማዋ እየታደሰ የሚገኘው የአስፋልት መንገድ ትራንስፖርትን ከማሳለጥ ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
በይርጋዓለም ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን የልማት እንቅስቃሴ ተከትሎ የኢንቨስትመንት እድገት በተለየ ሁኔታ ጨምሯል ነው ያሉት፡፡
የሕብረተሰቡን የተለያዩ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በከተሞችና ገጠር አከባቢዎች አስፈላጊው በጀት ተመድቦ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውንም የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት የዲጂታል ቴክኖሎጂና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ታደሰ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!