በ2ኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ የሚሳተፉ እንግዶች በሞጆ የዶሮ እርባታ ማዕከልን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ የሚሳተፉ እንግዶች በሞጆ የዶሮ እርባታ እና ዶሮ ማቀነባበሪያ ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡
የጉባዔው ተሳታፊዎች በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የምግብ ዋስትናን እና ሥርዓተ ምግብን ለማሻሻል እያከናወነቻቸው የሚገኙ ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጀመረቻቸው ጥረቶች በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበች ሲሆን÷ በዚህም በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ አሻራና ሌሎች ስኬታማ ሥራዎችን እያከናወነች ነው፡፡
ከተለያዩ ሀገራት በጉባዔው ለመሳተፍ የመጡ እንግዶ ዛሬ በሞጆ የዶሮ እርባታ እና ዶሮ ማቀነባበሪያ ማዕከላትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ የአቮካዶ ምርት ላይ እየሰራችው ያለውን ሥራ የጎበኙ ሲሆን÷ በዚህ ወቅትም የዶሮና የአቮካዶ ምርቶች ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለውጭ ገበያ እየቀረቡ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡
በሰዓዳ ጌታቸው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!