ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን በጅማ ከተማ አስጀምረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ባለፉት ዓመታት በተከናወነ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል፡፡
መርሐ ግብሩ ወደቀድመ ባሕላችን እንድንመለስ አስችሎናል ያሉት አቶ ሽመልስ ÷ ንቅናቄውን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
እንደ ኦሮሚያ ክልል በዛሬው ዕለት ለሚከናወነው የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የተሟላ ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል፡፡
የክልሉ ሕዝብም በነቂስ በመውጣት በመርሐ ግብሩ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡