Fana: At a Speed of Life!

አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የኢትዮጵያ መገለጫ ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ርስቱ ይርዳው አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ የምትታወቅበት መልካም መገለጫ ሆኗል አሉ፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች፤ ‹‹በመትከል ማንሰራራት›› በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ነው።

በዛሬው ዕለትም በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ሥነ ሥርዓት በመሳተፍ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡

አቶ ርስቱ ይርዳው በወቅቱ እንዳሉት÷ ባለፉት 7 ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተግባራት የደን ሀብት እንዲያድግ የሚያስችል ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።

አገልግሎቱ በተከታታይ በተካሄዱ መርሐ ግብሮች ከፍተኛ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው÷ ዘንድሮም በተመሳሳይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተመጣጠነ ዝናብ ለማግኘት፣ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ ለመኖር እንዲሁም በምግብ እራስን ለመቻል ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በንቅናቄው መላው ኢትዮጵያውያን እየተሳተፉ ነው ያሉት ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራሉ÷ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የምትታወቅበት መገለጫ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.