Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ8 ሺህ ቶን በላይ ማር ተመረተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ከ8 ሺህ ቶን በላይ ማር ማምረት ተችሏል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ 8 ሺህ 459 ቶን ማር ለማምረት ታቅዶ 8 ሺህ 157 ቶን ለማምረት ተችሏል።

በክልሉ የማር ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል 61 ሺህ 753 የንብ ቀፎዎችን ለማቅረብ ታቅዶ 59 ሺህ 706 ማቅረብ እንደተቻለም ጠቁመዋል።

በሁለት ዙር በተደረገው የማር ቆረጣ ከባህላዊ ቀፎ 13 ኪ.ግ ከሽግግር 36 ኪ.ግ እንዲሁም ከዘመናዊ ቀፎ 42 ኪ.ግ መገኘቱን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ ማር በማምረት ስራ 98 ሺህ 977 አርሶ አደሮችና ወጣቶች በምርት ሰንሰስት በማሳተፍ ተጠቃሚ ማድረግ ማቻሉንም አብራርተዋል።

በሌላ በኩል በ2018 በጀት ዓመት 8 ሺህ 628 ቶን ማር ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለማምረት መታቀዱን ገልጸው÷ 62 ሺህ 987 የጨፈቃ፣ የሽግግር እና የዘመናዊ የንብ ቀፎዎችን ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ 15 የግብርና ዘርፍ ኢኒሼቲቮች መኖራቸውን የገለጹት አቶ ኡስማን÷ የንብ ተደራሽነትና ማርታማነት ማሳደግ አንዱ እንደሆነና 3 በ 7 በሚል አንድ አቅም የሌለው አናቢ ቢያንስ ለመነሻ 3 ዘመናዊ እና 7 ባህላዊ ቀፎ እንዲኖራቸው ይደረጋል ብለዋል።

ይህም ከአንድ ዓመት በኋላ የማር ምርት ሽጦ የዘመናዊ ቀፎዎችን ቁጥር እያሳደገ እንዲሄድ ታስቦ የተዘጋጀ ኢኒሼቲቭ መሆኑን አንስተው÷ በዚህም ተደራሸነቱ እያደገ፣ ውጤታማነት እየጨመረ፣ ፍላጎት እያደገ እና ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን አመልክተዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.