Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ለኦቶና ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (ኦቶና ሆስፒታል) ከ6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የአርባ ምንጭ፣ ዲላ እና ጂንካ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በአካል ተገኝተው ድጋፉን ለሆስፒታሉ በማስረከብ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር)÷ የ90 ዓመት ታሪክ ያለው የኦቶና ሆስፒታል ባጋጠመው የእሳት አደጋ ጉዳት ማስተናገዱን አስታውሰዋል።

ሆስፒታሉን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በዮሴፍ ጩሩቆ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.