ማንቼስተር ዩናይትድ ቤንጃሚን ሼሽኮን ከደጋፊዎቹ ጋር አስተዋወቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ አዲሱ ፈራሚውን ቤንጃሚን ሼሽኮ በዛሬው ዕለት በኦልድትራፎርድ ከደጋፊዎቹ ጋር አስተዋውቋል፡፡
የ22 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች በዩናይትድ እስከ ፈረንጆቹ 2030 የሚያቆየውን የአምስት ዓመት ውል ፈርሟል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትዶች ከአርቢ ሌይፕዚሽ ላስፈረሙት ስሎቬኒያዊ ተጫዋች ዝውውር 85 ሚሊየን ዩሮ ወጪ አድርገዋል፡፡
በኦልድትራፎርድ ከፊዮረንቲና ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ ከጨዋታው መጀመር አስቀድሞ ሼሽኮን ከደጋፊዎች ጋር አስተዋውቋል፡፡
ዛሬ ፊርማውን ካኖረው ሼስኮ በተጨማሪ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቡን የተቀላቀሉት ማቲያስ ኩኛ፤ብሪያን ምቤሞ እና ዴጎ ሊኦን በይፋ ከዩናይትድ ደጋፊዎች ጋር ተዋውቀዋል፡፡
በተጨማሪም የቀድሞ የክለቡ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሂያ የክብር አቀባበል ተደርጎለታል፡፡