Fana: At a Speed of Life!

ዴሞክራሲያችን ኢትዮጵያዊ መከባበርና ባህል ላይ የተመሰረተ መሆን ይጠበቅበታል – ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዴሞክራሲያችን ኢትዮጵያዊ መከባበር እና ባህል ላይ መሰረቱን ያደረገ መሆን ይጠበቅበታል አሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)።

ሚኒስትሩ ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት÷ ኢትዮጵያዊያንን ሊያግባባ የሚችል የዴሞክራሲ አማራጭ ይዞ መጓዝ ይገባል፡፡

ኢትዮጵያዊያን ያላቸው የገዳ ሥርዓት እሴቶች፣ ግጭትን በሰላማዊ መንገድ በእርቅ የመጨረስ ባህል እንዲሁም “በህግ አምላክ” ሲባል የህግ የበላይነትን በግልጽ የሚያሳይ እሴት የዴሞክራሲ መገለጫዎች ናቸው ብለዋል፡፡

እነዚህን ሀገር በቀል እውቀቶች እና እሴቶች ዘመኑ ከደረሰበት እውቀት ጋር አዋህዶ፣ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችን ቀስሞ እና ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ ለኢትዮጵያ ምቹ የሆነ ዴሞክራሲን ማስፈን ይጠበቃልም ነው ያሉት፡፡

የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው የኢትዮጵያዊያንን ባህል፣ ታሪክ፣ እሴት እና ሥነ ልቦና ማዕከል ያደረገ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጥያቄ ሲነሳ የተሞከረው ዴሞክራሲ ከኢትዮጵያ ነባራዊ እውነት ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ስኬታማ አልሆነም ያሉት ተስፋዬ (ዶ/ር)÷ የምንተገብረውን ዴሞክራሲ ኢትዮጵያዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

በርካታ ሀገራት የራሳቸው ባህል እና እሴት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲ ስለገነቡ ስኬታማ መሆናቸውን አንስተው÷ ኢትዮጵያዊያንም ኢትዮጵያዊ የሆነ ዴሞክራሲን መፈለግ አለብን ብለዋል።

ዴሞክራሲ በሁለት መልኩ ሊታይ እንደሚችል ጠቁመው÷ ይሄውም የአብላጫ እና የመግባባት ዴሞክራሲ ነው ሲሉ አብራርተዋል።

ሀገራዊ መተማመንን ለመፍጠር የመግባባት ዴሞክራሲን መከተል እንደሚገባ ገልጸው÷ ይህም በተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አንድ ደረጃ ከፍ ይላል የሚል እምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

በብርሃኑ አበራ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.