Fana: At a Speed of Life!

የኮንስትራክሽን ተቋራጮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ከ20 በላይ የኮንስትራክሽን ተቋራጮች ጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲሰሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው አሉ፡፡

በፈረንጆቹ ከ2025 እስከ 2050 ድረስ የሚተገበር የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭ ይፋ ማድረጊያ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ተካሂዷል።

በሥነ ስርዓቱ ላይ ሚኒስትሯ እንዳሉት፤ በ10 ዓመቱ ዕቅድ ኢንዱስትሪ የስራ ዕድል እንዲፈጥር እና ቀጣይነት ያለው የዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን እንዲያረጋግጥ እየተሰራ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት የሀገር ውስጥ ተቋራጮች ከ70 በላይ ከተሞች ላይ የኮሪደር ልማት ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ በቀጣይ ዘርፉን በጥራት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

ኢኒሼቲቩ ቅንጅትን የሚያጠናክር እና የኢትዮጵያ ኩባንያዎች በአፍሪካ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የምዘና፣ የዕውቅና እና የተጠያቂነት አሰራርን በመዘርጋት ሀገራችን በዘርፉ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችል ነው ብለዋል።

እስከ 20 ተቋራጮች በቀጣይ ጥቂት ዓመታት በጎረቤት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ይሰራል ነው ያሉት።

በኢንዱስትሪው እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት የተቋማት እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

በለይኩን ዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.