በልጃገረዶች የሚከበሩት የአብሮነት በዓላት አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል…
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል በዓላት በቀጣይ ይበልጥ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ መጠበቅና መንከባከብ ይገባል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በክረምት ወራት በልጃገረዶች ከሚከበሩ የአብሮነት ክብረ በዓላት መካከል ናቸው ብለዋል።
ልጃገረዶች በተለያዩ ባሕላዊ አልባሳት አምረው፣ በባሕላዊ የፀጉር አሰራር ደምቀውና ተውበው በነጻነት አደባባይ ወጥተው ባህልና አብሮነታቸውን ሲያሳዩ መመልከት እጅግ አስደሳች ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እነዚህ በዓላት በቀጣይ የበለጠ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡