Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል 150 ሺህ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች የሚገኙ 150 ሺህ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጀምሯል።
የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታውን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።
አቶ ሙስጠፌ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ፕሮጀክቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የጅግጅጋ ከተማ ሕዝብ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፍላጎት ተደራሽ ማድረግ ያስችላል፡፡
በተለይም በበጋ ወራት ሊከሰት የሚችልን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረት መፍታት እንደሚያስችል ነው የገለጹት፡፡
ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ አጠናቅቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ተገቢው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።
በፕሮጀክቱ 20 ጥልቅ የመጠጥ ውሃ ጉድጓዶች የሚቆፈሩ ሲሆን÷ ሰባቱ ለጅግጅጋ ከተማና አካባቢው አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡
በተስፋዬ ሃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.