Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሳይፕረስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳይፕረስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮንስታንቲኖስ ኮምቦስ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የነበረንን ቆይታ አጠናቀን ወደ አዲስ አበባ ተመልሰን የሳይፕረስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኮንስታንቲኖስ ኮምቦስ እና የልዑካን ቡድናቸውን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብለናል ብለዋል።

ሁለቱ ሀገሮቻችን የዲፕሎማቲክ ግንኙነታችንን ለማጠናከር ብሎም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትብብሮችን ለማጎልበት ጠንካራ ፍላጎት አለን ሲሉም ገልጸዋል።

በመሆኑም እነዚህን የጋራ አላማዎች ለማራመድ የሚጠቅሙንን ሰፊ አድማስ ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.