ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስሎቬኒያ ሉብሊያ ማራቶን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በስሎቬኒያ ሉብሊያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡
በወንዶች በተደረገው ውድድር አትሌት ሃፍታሙ አባዲ 2 ሰዓት ከ 06 ደቂቃ ከ52 ሰኮንድ በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቋል።
በውድድሩ ላይ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ከማል ሁሴን ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሷል፡፡
በሴቶች ደግሞ አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ 2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ ከ46 ሰኮንድ በመግባት ነው ውድድሯን በአንደኝነት ያጠናቀቀችው፡፡