Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 17ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በጉባዔው የ2017 እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ሲሆን፥ በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ ገቢው ከ357 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት 27 ሚሊየን ብር ኪሳራ ያጋጠመው ፌዴሬሽኑ፥ ባለፈው በጀት ዓመት 59 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተገልጿል፡፡

የኢእፌ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ክለቦች የፊፋን የክለብ ላይሰንሲንግ መስፈርቶች እንዲያሟሉ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ወንዶችና ሴቶች ዋና ብሔራዊ ቡድኖች ለአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ከ123 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉንም አንስተዋል።

በሙባረክ ፋንታው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.