መንግሥት ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎችን አከናውኗል – ሙፈሪሃት ካሚል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት ሕዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎችን አከናውኗል አሉ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል።
“የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ የፌዴራልና ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ሕዝባዊ ውይይት አካሂደዋል።
ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት በጎንደር ከተማ ዓይን ገላጭ የልማት ስራዎች እንዲሁም ሀገራዊ መልክ ያላቸውን የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
መንግሥት ኢትዮጵያን የመሰለ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረው÷ በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮችን እየፈታ ጎን ለጎን ደግሞ ሕዝቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደርና የመልማት ጥያቄዎች እየመለሰ ይገኛልም ነው ያሉት።
ባለፉት 8 ዓመታት በሁሉም ማዕዘናት አካታች የሆነ የልማት ስራዎች እንደሀገር መፈፀሙን ጠቅሰው÷ የተሟላ የልማት ስራ በቀጣይ ለማከናወን ከሕዝቡ ጋር ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አመላክተዋል።
መንግሥት የሰላም ችግሮች እንዲፈቱ የጀመራቸው ጥረቶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው÷ የልማት ስራዎችም ሁሉንም አካባቢ አሳታፊ በሆነ መንገድ እየተሰራ እንደሆነና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በጎንደር ከተማ ከውሃ ጋር በተያያዘ የከተማው ህዝብ የሚያነሳውን ጥያቄ ለመመለስ በፌደራል መንግሥት የተጀመሩ ጥረቶች በጥሩ ሁኔታ መቀጠላቸውንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኛው በበኩላቸው፤ ከተማዋ በቀደሙት ጊዜያት ተነፍጋ የቆየችው የልማት ስራዎች አሁን ላይ በተሟላ መንገድ እየተፈፀሙ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
እንደሀገር የተጀመሩ የልማት ስራዎች ጎንደር ከተማን አካቶ እየተተገበረ እንደሚገኝ በመግልጽ÷ በቀጣይም የተሻለ ስራ በከተማዋ ለማከናወን እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በውይይቱ ሚኒስትሯን ጨምሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።
በምናለ አየነው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!