Fana: At a Speed of Life!

ሀድያ ሆሳዕና ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሀድያ ሆሳዕናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ጫላ ተሺታ አስቆጥሯል፡፡

ሀድያ ሆሳዕና በሊጉ ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን ሲያሳካ ሀዋሳ ከተማ በበኩሉ ከሁለት ተከታታይ ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

በተመሳሳይ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከሸገር ከተማ ይገናኛሉ፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም መደረግ የጀመረው የምድረ ገነት ሽረ እና አዳማ ከተማ ጨዋታ እስካሁን ግብ አልተቆጠረበትም፡፡

ቀን 7 ሰዓት ላይ በዚሁ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ነገሌ አርሲ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 ማሸነፉ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.