Fana: At a Speed of Life!

ለመጀመሪያ ጊዜ ቀዝቃዛ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀዝቃዛ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በባቡርና በመርከብ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ጀመረች።

አቮካዶ የጫነ የመጀመሪያው ኮንቴነርም ዛሬ ከሞጆ ደረቅ ወደብ ወደ አውሮፓ ለሙከራ ተልኳል ነው የተባለው ።

የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ምርቶቹ ለውጭ ገበያ መቅረባቸው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮችና ወጣቶች ምርቶቻቸውን ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ አንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።

እንዲሁም ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ዕድል በመፍጠር ረገድም ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

በቀጣይም አርሶ አደሩ የግብርና ምርቶቹን ጥራታቸውን እንደጠበቁና ሳይበላሹ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ለማድረግ እንተጋለን ብለዋል።

ለዚህም የባቡርና መርከብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ምርቱ በሚመረትበት ሥፍራ በትኩስነቱ እንዲመጣ የማቀዝቀዣአገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች እንደሚቀርቡ ሚኒስትሯ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዚህም ቀጣይነት ያለው የምርት አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነትና የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.