Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሀገራዊ ለውጡን 8ኛ ዓመት የሚዘክር የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት በማስመልከት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው፡፡

የድጋፍ ሰልፎቹ በክልሉ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ እና ሳውላ ከተሞች እየተካሄዱ ሲሆን፥ በለውጡ መንግስት የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚገልጹ መልዕክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ፡፡

ሰልፈኞቹ ካስተላለፏቸው መልዕክቶች መካከል “ቀጣዩ ጀግንነታችን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነታችን፣ ስልጣንን በአፈሙዝ ለመጨበጥ ማሰብ ጊዜው ያለፈበት ነው፣ መጋቢት 24 – የኢትዮጵያ ዳግም ልደትና የአሸናፊነት ምዕራፍ” የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በኢብራሂም ባዲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.