ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከቡሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከቡሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት አንጀሊን ንድያይሺሚዬ ጋር ተወያይተዋል።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የቡሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት በብሔራዊ ቤተመንግስት ተቀብዬ ጉብኝት አድርገናል ብለዋል።
በነበረን ቆይታም በምንሰራቸው የጋራ ስራዎች እና የቀጣይ ትብብሮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ነበረን ሲሉ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።