በጎሮ ጉቱ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ጉቱ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አልፏል።
አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ሲጓዝ በነበረ ኮንቴነር የጫነ ተሽከርካሪ ላይ መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
በተከሰተው አደጋም እስካሁን የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ነው የተገለጸው፡፡