Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት በማህበራዊ ዘርፍ ላይ ያተኮረ መድረክ እየተካሄደ ነው ‎

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በማህበራዊ ዘርፍ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

“የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ላይ በዘርፉ ባለፉት ስምንት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡

‎መድረኩ በተለይም በትምህርት፣ ጤና፣ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በባህል፤ በኪነ-ጥበብና ስፖርት እንዲሁም በሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች የተመዘገቡ ውጤቶች በስፋት የሚተነተኑበት መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.