ቶተንሃም ሆትስፐር አንዲ ሮበርትሰንን አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቶተንሃም ሆትስፐር ስኮትላንዳዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች አንዲ ሮበርትሰን ወደ ስብስቡ መቀላቀሉን ይፋ አድርጓል፡፡
አንዲ ሮበርትሰን ከ9 ዓመታት የአንፊልድ ቆይታ በኋላ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሊቨርፑል ጋር መለያየቱ ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐር የ32 ዓመቱን ተጫዋች በነጻ ዝውውር የግሉ አድርጓል፡፡
የቶተንሃም አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ አንዲ ሮበርትሰን የሚያደንቁት ተጫዋች መሆኑን ጠቅሰው÷ በቡድናቸው ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ አብራርተዋል፡፡
ስኮትላንዳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች አንዲ ሮበርትስን በሊቨርፑል ቆይታው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡
ቶተንሃም ሆትስፐር በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሊጉ 17ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡