Fana: At a Speed of Life!

ኅብረ ብሔራዊ ውበትና የኢትዮጵያ ታላቅነት

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መኖሪያ፤ የባህል፣ የቋንቋ እና የቅርስ ህያው ጎጆ ናት።
ይህ እንደ ማግና ሸማ የተሸመነ ብዝኃነታችን የድክመቷ ሳይሆን፤ የጽናትና እና የታላቅነቷ ምንጭ ነው።
ኅብረ ብሔራዊነት ማለት የልዩነቶች ውበት የሚደምቅበት፤ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህል፣ ቋንቋ እና ማንነት እኩል አክብሮት የሚያገኝበት፣ እንዲሁም በጋራ ሀገራዊ ማዕቀፍ ውስጥ አብሮነት የሚጠናከርበት ህያው የኑሮ መንገድ ነው።
እነዚህ እሴቶች በፈተናዎች ውስጥ የማለፍ፣ የመረዳዳት እና በአንድነት የመቆም ተፈጥሯዊ ጸጋዎች ናቸው።
ዛሬ ኢትዮጵያ የህዝቧን አንድነት እና እምቅ አቅም በመጠቀም፤ ኅብርን በቃላት ደረጃ ብቻ ሳይሆን፤ በተግባር የሚገልጡ ታላላቅ ሀገራዊ ሁነቶችን እውን እያደረገች ትገኛለች።
ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር ከመጀመር እስከ መፈጸም በመድረስ የጽኑ ሰላም ሀገራዊ መግባባትን መሰረት በመጣል ኅብርን አጠንክሮ የመሄድ ርምጃው ተጀምሯል፡፡
ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ፣ ጽዱ እና ዘመናዊ በማድረግ የዜጎችን የዕለት ተዕለት የኑሮ ጥራት ማሻሻል ተችሏል።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎት አቅም ያላቸው አቅም የሌላቸውን የሚያግዙበት፣ የሰው ልጅ ክብር የሚጠበቅበት እና የእርስ በእርስ መረዳዳት ባህል በላቀ ደረጃ የጎለበተበት ማኅበራዊ እሴት ሆኗል።
የተፈጥሮ አካባቢን በመንከባከብ ለነገው ትውልድ አረንጓዴ እና ምቹ ሀገርን የማስረከብ ታላቅ የተፈጥሮ ጥበቃ እንቅስቃሴዎች በህብረትና በስኬት መከናወናቸውን ቀጥለዋል።
እነዚህ ሁሉ የሚያሳዩት በአንድነት መቆም ከተቻለ የጋራ ትርክቶችን ወደ ታላቅ የወል ስኬት ማሸጋገር እንደሚቻል በተግባር ያረጋገጠ ነው።
የኅብር ቀን የዚሁ የጋራ ጥረታችን፣ የጽናታችን፣ የኅብረ ብሔራዊነታችን እና የብልጽግና ጉዟችን ህያው ማረጋገጫ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቀኑን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በመገንባት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ አካታች የሆነች፣ በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች፣ የአብሮነትና መረዳዳት ባህል የጎለበተባት ጠንካራ ሀገር ነች ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያውያን የጋራ ታላቅነትና እምቅ አቅም በተግባር እየተረጋገጠ በአንድነት ወደ ብልጽግና የሚደረገው ጉዞ እየቀጠለ ነው፡፡
በመልካም ፈቃዱ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.