በትግራይ ክልል የተቋረጡ አገልግሎቶችን ለማስጀመር በቅንጅት እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል የተቋረጡ አገልግሎቶችን ለማስጀመር የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር ከፌዴራል ምንግሥት እና ከህዝቡ ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ነው።
የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የኢኮኖሚና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ ቴዎድሮስ አረጋይ (ዶ/ር)፤ በክልሉ የተጓደሉ አገልግሎቶችን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ባለአደራ አስተዳደሩ ስራ ከጀመረ በኋላ ሰላምና ጸጥታ እንዲሰፍን የማረጋጋት ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህ ባሻገር የተቋረጡ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ ለማስቻል ከህዝቡና ከፌዴራል መንግሥት ጋር የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ አንስተዋል።
ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት በማድረግ ሰላም እንዲጠበቅ በጋራ እየሰራን ነው ያሉት ቴዎድሮስ አረጋይ (ዶ/ር)፤ የመማር ማስተማር አገልግሎት እንዲመለስ ቅድመ ዝግጅት እያደረግን ነው ብለዋል።
አሁን ላይ ንግድን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
ህዝባችን ሰላም ሰላም ፈላጊ ነው በማለት ገልጸው፤ አለመታደል ሆኖ ብዙ መከራ እንዲያሳልፍ ተደርጓል ብለዋል።
የተጓደሉ ነገሮችን ለማሟላት ከህብረተሰቡ እና ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ህብረተሰቡ ከባለአደራ አስተዳደሩ ጎን ሆኖ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ጠቁመዋል።
አስተዳደራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ቢሮዎች ሆነ ተብሎ እንዲወድሙ የተደረገ ቢሆንም ከጥገናው ጎን ለጎን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በትዕግስት ግዛቸው