Fana: At a Speed of Life!

የሚገነቡት ፕሮጀክቶች የመደመር መንግሥት እሳቤዎችን ማዕከል ያደረጉ ናቸው – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሚገነቡት ፕሮጀክቶች የመደመር መንግሥት እሳቤዎችን ማዕከል ያደረጉ ናቸው አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፡፡

አቶ አረጋ ከበደ የመገጭ ግድብ ፕሮጀክት ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ፕሮጀክቱ ለሚገኝበት አካባቢና ማህረሰብ እጅግ የምስራች ይዞ የመጣ ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲስተጓጎል እና ሲንከባለል የነበረ ቢሆንም፤ የመደመር መንግሥት ያደሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማረምና የማስተካከል ዋነኛ መገለጫው መሆኑን ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃ የዘመናት ችግር በዘላቂነት የሚያቃልልና ለአሳ ሀብት ልማት፣ የሀይቅና የወንዝ ዳርቻ መሰረት አድርገው ለሚገነቡ ሆቴሎችና ሪዞርቶች እንዲሁም ለከተሞች የቱሪስት መዳረሻ በመሆን የሚያለግል ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በፌደራል መንግሥት እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ለክልሉ ህዝብና መንግሥት ልዩ ትርጉማ እንዳለው ጠቁመው፤ ፕሮጀክቶቹም የመደመር መንግሥት እሳቤዎችን ማዕከል ያደረጉ ናቸው ብለዋል፡፡

በልማት ሂደት በበቂ ሁኔታ የማይጠቀሙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

የመገጭ መስኖ ግድብ 17 ሺህ ሄክታር መሬትን በመስኖ ማልማት የሚያስችል፣ ለ25 ሺህ የአካባቢው አርሶ አደሮች በልማቱ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ግድቡ ለከተማችን ጎንደር አስተማማኝ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በትዕግስት ግዛቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.