ጠ/ሚ ዐቢይና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የእንጦጦ ፓርክን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የእንጦጦ ፓርክን ጎበኙ።
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዚህ ሳምንት የተመረቀውን የእንጦጦ ፓርክ ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት፣ ፕሮጀክቱ በመሰራት ላይ እያለ እና የተጠናቀቀውን የፓርክ ጉብኝት ጨምሮ ለሶስተኛ ጊዜ እንደጎበኙት ኢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።
መሪዎቹ ባለፉት ሁለት ቀናት የኮይሻ እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባለፈው ሰኞ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡