Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 712 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትጵዮያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 121 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 712 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በዚህም በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 86 ሺህ 430 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 858 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 40 ሺህ 165 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

 

እንዲሁም በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የ7 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን አጠቃላይ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 312 ደርሷል።

በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 370 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.