Fana: At a Speed of Life!

ለአራት የህክምና ላቦራቶሪዎች የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አስፈላጊውን መስፈርት ላሟሉ አራት የህክምና ላቦራቶሪዎች አክሪዲቴሽን አገልግሎት መስጠቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
ተቋማቱም የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምሀራን ሪፊራል ሆስፒታል ፣ ደብረብርሃን ሪፊራል ሆስፒታል ላቦራቶሪ፣ የጦር ሀይሎች አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላቦራቶሪ እና ሻሸመኔ ሪፊራል ሆስፒታል ናቸው።
ፅህፈት ቤቱ አገልግሎቱ የሰጣቸው የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከመከሰቱ በፊት የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ለማግኘት ማመልከቻ አስገብተው የሰነድ ምርመራ እና የመስክ ግምገማ ለተካሄደባቸው ተቋማት መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።
በዚህም ተቋማቱ በህክምና ዘርፍ በISO 15189 የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአክሪዲቴሽን አፅዳቂ ኮሚቴ ፀድቆላቸዋል ተብሏል።
ተቋማቱ አሁን ላይ የአክሪዲቴሽን ተጠቃሚ የሆኑት በአንድ የፍተሻ ወሰን መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ የፍተሻ አድማሳቸውን በማስፋት አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ብሏል ፅህፈት ቤቱ በመግለጫው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.