Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አስመራ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ሲያደርጉት የነበረውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አስመራ ተመለሱ።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ልዑካቸው ባሳለፍነው ሰኞ ነበር በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በጅማ ከተማ የጀመሩት።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እና ልዑካቸው በኢትዮጵያ ቆይታቸው የህዳሴ ግድብን ጨምሮ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “በኢትዮጵያ ካካሄዱት የሦስት ቀን ውጤታማ የሥራ ጉብኝት እንዲሁም በልዩ ልዩ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ካተኮረ ውይይት በኋላ፣ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ እና ለልዑካን ቡድናቸው አሸኛኘት አድርገናል” ብለዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.