Fana: At a Speed of Life!

357 ዜጎች ካሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 357 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ዛሬ ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ መስፍን ገብረማርያምን ጨምሮ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ሃለፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ከዛሬዎቹ ተመላሾች ውስጥ 262ቱ ሴቶች ሲሆኑ 95ቱ ደግሞ ህጻናት መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.