የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት ምስጋና አቀረበ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለገበታ ለሀገር ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብለው የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት ምስጋና አቀረበ፡፡
ፅህፈት ቤቱ ኮይሻን፣ ጎርጎራን እና ወንጪን በጋራ ለማልማት የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ገንዘብ ገቢ ላደረጉ ተቋማት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
እስካሁን ገንዘብ በማስገባት የተዘረዘሩ ተቋማት
ዘመን ባንክ – 10 ሚሊየን ብር
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ – 10 ሚሊየን ብር
አዲስ የብድርና ቁጠባ ተቋም – 5 ሚሊየን ብር
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር – 5 ሚሊየን ብር
አባይ ባንክ አክሲዮን ማህበር – 10 ሚሊየን ብር
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማህበር – 5 ሚሊየን ብር
ወጋገን ባንክ – 10 ሚሊየን ብር
ሌሎች ተሳታፊ ተቋማትም የ5 እና የ10 ሚሊየን ብር አስተዋጽኦዋቸውን ባንክ ያስገቡበትን ደረሰኝ በdineforethiopia@pmo.gov.et የኢሜል አድራሻ እንዲልኩም ጠይቋል።