የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ በኢትዮጵያ የአውስትራሊያው አምባሳደር ፒተር ዶይል ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ አምባሳደር ፒተር ዶይል ጋር ተወያይተዋል።
ኢትዮጵያ በእድገት እቅዷ ትኩረት ከምታደርግባቸው ዘርፎች አንዱ የመአድን ልማት እንደሆነ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተናገረዋል።
ዘርፉን በዘመናዊ መልኩ ለመገንባትም ከተለያዩ ሀገራት ጋር በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።
አምባሳደሩ በበኩላቸው አውስትራሊያ በማዕድን ልማት ያላትን ስኬታማነት ለኢትዮጵያ እንደምታካፍል ገልፀዋል።
ዘርፉን ለማገዝም ሀገራቸው የተለያዩ ድጋፎችን እንደምታደርግም አምባሳደር ፒተር ዶይል ተናግረዋል።
አምባሳደሩ ህዳር ወር በአውስራሊያ በሚደረገው “Africa Down under conference” ላይ ሚኒስትሩ ኡማ እንዲሳተፉ ግብዣ እንዳቀረቡላቸው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።