በምስራቅ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 207 ሺህ 454 ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቅ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 207 ሺህ 454 ደረሰ፡፡
በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሰባት ሃገራት ውስጥ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ 104 ሺህ 427 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ÷ 1 ሺህ 607 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
እንዲሁም በሱዳን 15 ሺህ 299 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው 1 ሺህ179 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡
በኬንያ 74 ሺህ 145 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ÷1 ሺህ 330 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡
በሶማሊያ 4 ሺህ 382 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተነገረ ሲሆን÷ በሃገሪቱ 108 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
እንዲሁም በጁቡቲ 5 ሺህ 658 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ÷ 61 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡
በኤርትራ ደግሞ 527 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ÷ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወቱ ያለፈ ሰው ግን የለም፡፡