አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በተመድ ከአሜሪካ አምባሳደር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት /ተመድ/ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በተመድ ከአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ጋር መከሩ፡፡
በውይይታቸው ወቅትም በትግራይ ክልል ስላለው ሰብአዊ ድጋፍ ላይ መምከራቸውም አምባሳደር ታዬ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የጋራ በሆኑ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ሃገራቱ በተመድ ያላቸውን ትብብርና ግንኙነት ለማጠናከርም ተስማምተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!