Fana: At a Speed of Life!

የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች ነጻ የአየር ሰዓት ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለተመዘገቡ የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች ነጻ የአየር ሰዓት ድልድል ይፋ አድርጓል፡፡

ቦርዱ ድልድሉን ይፋ ያደረገው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በግል ዕጩነት ለመወዳደር የተመዘገቡ የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ÷ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በጊዜ ሠሌዳው መሠረት ለማካሄድ የቅድመ ምርጫ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡

የግል እጩዎችን የአየር ሰዓት መደልደል የቅደመ ሥራው አንዱ አካል መሆኑን ጠቅሰው ÷ የግል ዕጩዎቹ  የምረጡኝ ቅስቀሳ ሃላፊነት በተሞላበትና ሕግን በተከተለ መንገድ መከወን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በድልድሉ መሰረት ለወንድ የግል ዕጩ15 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው አንድ የቴሌቪዥን፣ አንድ የሬዲዮና አንድ የጋዜጣ አምድ በመረጣቸው መገናኛ ብዙኃን ላይ ያስተላልፋል፡፡

የግል ዕጩዋ ሴት ከሆነች በሦስት መገናኛ ብዙኃ የሥርጭት አማራጮች የሚሰጠውን ነጻ የአየር ሰዓት በመረጠችው የሥርጭት አማራጭ እንድታስተላልፍ አንድ ተጨማሪ እድል ይሰጣል፡፡

ሴት አካል ጉዳተኛ ከሆነች ደግሞ ምርጫው ወደ አምስት ከፍ እንደሚል መገለጹን የቦርዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ ወንድ አካል ጉዳተኛ ዕጩ ከሆነ በሦስት የሥርጭት አማራጮች ለአንድ ጊዜ የነበረው ነጻ የአየር ሰዓት ድልድል በመረጠው የሥርጭት አማራጭ ላይ አንድ ተጨማሪ ዕድል ይሰጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.