በአፋር ዘግይቶ የተጀመረው የመራጮች ምዝገባ በ1 ሺህ 432 ጣቢያዎች እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ለ6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በ1ሺህ 432 ጣቢያዎች የመራጮች ምዘገባ እየተካሄደ መሆኑን በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአፋር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ጣሃ አሊ እንደገለጹት፤ የመራጮች ምዝገባ በተለያዩ ምክንያቶች ከተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ዘግይቶ ተጀምሯል።
ከጸጥታ፣ ትራንስፖርትና መሰል ችግሮች ጋር ተያይዞ የምርጫ ቁሳቁሶች በወቅቱ ወደ ምርጫ ጣቢዎች መድረስ ባለመቻላቸው የመራጮች ምዘገባ የምርጫ ቦርድ ካስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ዘግይቶ መጀመሩን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ቦርዱ ከመንግስት ጋር በመተባበር ባደረገው ጥረት በክልሉ በተቋቋሙ ጣቢያዎች አስፈላጊው ቅጾች ተሟልተው ካለፈው አርብ ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!