Fana: At a Speed of Life!

የፖሊስ መዋቅር፤የጦር መሳሪያ ዝውውር የተመለከቱትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፖሊስ ሙያና በህግ ማስከበር ዙሪያ  የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨረሲቲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ጥናታዊ ጽሁፎችን ከሚያዚያ ከ28 እስከ 29 ቀን 2013 ዓ.ም  አቀረበ፡፡

ኢንስቲዩቱ የፖሊስ አገልግሎቶች እና አሰራሮችን ለማሻሻል ከዚህ በፊት የነበሩ አሰራሮችን መነሻ በማድረግና በተግባር ከሚያጋጥሙ ችግሮች በመነሳት ዘመናዊ የፖሊስ ተቋም ለመገንባት እየሰራ ያለ ተቋም መሆኑ ተገጿል፡፡

ከቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፎች መካከል በፖሊስ መዋቅር፣ በጦር መሳሪያ ዝውውር ፣ በበማህበረሰብ ፖሊሲግ አተገባበርና አጋጣሚዎች፣ በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደትና በህግ ማስከበር የፖሊስ ሚና ፣ በጾታዊ ጥቃትና የኤች-አይቪ ስርጭትን በመቀነስ እና በፖሊስ ደረጃዎች ዙሪያ የቀረቡ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮምሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ፤ ባደረጉት ንግግር ጥናታዊ ጽሁፎቹ በፖሊስ ሙያና በህግ ማስከበር ዙሪያ  ለቀጣይ ተልዕኮ ግብኣት እንደሚሆኑና ግንዛቤ እንደሚያስጨብጡ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የልምድ ልውውጥን በማዳበር፣ ያለፉ አሰራሮችና አፈጻጸሞችን እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በመለየት ለቀጣይ ሀገራዊ ተልዕኮዎችና አፈጻጸሞች የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጡና ለስራ የሚያነሳሱ ናቸው  ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ዩኒቨረሲቲ ኮሌጅና የፌደራል ቴክኒክ ሙያና ስልጠና ኤጀንሲ በጋራ የፖሊስን ሙያና ግንዛቤ ለማሳደግና ወጥ የሆነ የፖሊስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የፖሊስ ስታንዳርድ መጽሀፍ አሳትመው ለፌደራል ፖሊስ፤ለከተማ መስተዳድርና ለክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች መስጠታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጥናታዊ ጽሁፎችቹ የቀረቡት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች፣ የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.