Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ድርድር እንደገና ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ድርድር እንደገና መጀመሯ ተገለፀ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚና ፖሊሲ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመሆን ስታደርገው የነበረውን ድርድር ከዓመታት ቀይታ በኋላ መጀመሯን በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

አማካሪው ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት በመደገፍ ላይ ለሚገኙት የወቅቱ የድርጅቱ ጄኔራል ዳይሬክተር ሮቤርቶ አዜቬዶ ምስጋና አቅርበዋል።

ድርድሩን ለማካሄድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ መራጭነት በአቶ ማሞ ምህረቱ የሚመራ 10 የኮሚቴ አባላት ከወራት በፊት መመረጣቸው የሚታወስ ነው።

እነዚህ የኮሚቴ አባላት ከብሄራዊ ባንክ፣ ከብሄራዊ የፕላንና ልማት ኮሚሽን፣ ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ናቸው።

የኮሚቴው አባላት በእቃዎች እና በአገልግሎት ዘርፍ የሚደረጉ ስምምነቶች በመመካከር እንደሚወስኑ ነው የተነገረው።

የንግድ እና የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ሀገሪቱ ለጀመረችው የለውጥ ጉዞ ውጤታማነት ትልቅ አጋዥ ናቸው ተብሏል።

የንግድ እና የኢንቨስትመንት ስምምነቶችለኢንዱስትሪ እድገት፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ለተዘጋጁ ስትራቴጅዎች ደጋፈ መሆናቸውን የኢኮኖሚ አማካሪው አቶ ምህረቱ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.