በወሎ ግንባር በርካታ የአሸባሪው ታጣቂዎች እየተደመሰሱና እጅ እየሰጡ ነው- የግንባሩ የጦር መኮንኖች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን ህወሓት በመደምሰስ አኩሪ ጀብዱ እየፈጸሙ እንደሚገኙ በወሎ ግንባር የተሰለፉ የጦር መኮንኖች ተናገሩ።
በግንባሩ የጠላት መሳሪያዎችና ታጣቂዎች እየተማረኩና እየተደመሰሱ ጠላት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን ገልጸዋል።
የ13ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሬጅመንት አዛዥ፥ ሰራዊቱ አሸባሪውን ህወሓት በገባባቸው ሁሉ እየተከታተለ በመቅበር ላይ ነው ብለዋል።
በግንባሩ በርካታ የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች እየተደመሰሱ፣ እየተማረኩና እጅ እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።
አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ወሎ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ግፍና በደል በመፈፀም ላይ መሆኑን ጠቅሰው፥ በሰራዊቱና በየፀጥታ ሃይሎች “ድባቅ ይመታል” ሲሉ አረጋግጠዋል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት በተሰለፈባቸው ውጊያዎች ሁሉ በጀግንነት ጀብድ እየፈፀመና ድልን እየተጎናፀፈ መሆኑን የ13ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሬጅመንት ምክትል አዛዥ ገልጸዋል።
ሰራዊቱ እያደረገ ካለው ጀግንነት በተጨማሪ ህዝቡ ከፍተኛ ድጋፍና እገዛ እያደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት በአሸባሪው ህወሓት ግፍና ስቃይ እየደረሰበት ያለውን ህዝብ ነፃ ለማውጣት መዘጋጀቱንም አረጋግጠዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!



0
People Reached
1,033
Engagements
Boost Post
930
40 Comments
59 Shares
Like
Comment
Share
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!



0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share