የመንግሥት እና የመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኀላፊዎች ማይጠብሪ ግንባር ገቡ
አዲስ አበባ ፣መስከረም 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግሥት እና የመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኀላፊዎች ጀግኖችን ለማዬትና በአሸባሪው የትህነግ ቡድን የተጎዱ ወገኖችን ለመጠየቅ ማይጠብሪ ግንባር ገብተዋል።
የመንግሥት እና የመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኀላፊዎች በማይጠበሪ ግንባር በአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን ነዋሪዎችና በጭና የተገደሉ የንጹሐን ቤተሰቦችን ይጠይቃሉ። በግንባሩ ያሉ ጀግኖችንም ይጎበኛሉ።
በማይጠብሪ ግንባር የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፥ የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፣ የብልጽግና ጽሕፈት ቤት የሕዝብና ውጭ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አማካሪ ሚኒስትር ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ጨምሮ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት መሪዎች ናቸው የተገኙት።
መሪዎቹ በማይጠብሪ ግንባር ሲገቡ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ያለዓለም ፈንታሁን አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!



0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share