ዘራፊና ገዳይ የሆነውን የሸኔ ቡድን የጉጂ ኦሮሞ አባገዳዎች አወገዙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ጉጂ ህዝብ ዘራፊና ገዳይ የሆነውን የሸኔ ቡድን አሳልፎ እንዲሰጥ የጉጂ ኦሮሞ አባገዳዎች ውሳኔ አሳለፉ፡፡
የጉጂ ኦሮሞ አባገዳዎች የሀገር ሽማግሌዎችና የዞኑ ነዋሪዎች ሽብርተኛው ሸኔ በንጹሀን ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆም እንዲቻል በቡሌ ሆራ ከተማ መክረዋል፡፡
አሸባሪው ሸኔ በንጹሀን የጉጂ ኦሮሞ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ላይ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑን በምክክር መድረኩ ተነስቷል፡፡
በመድረኩ አሸባሪው ሸኔ በኦሮሞ ጠላትነት እንዲፈረጅና ህዝቡም የቡድኑን አባላት አሳልፎ ለመንግስት እንዲሰጥ ውሳኔ ተላልፏል።
የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ሰብሳቢና የጉጂ ኦሮሞ አባገዳ ጂሎ ማእኖ በወቅቱ እንደተናገሩት አሸባሪው ሸኔ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያደረሰ ባለው ጥቃት በየዕለቱ የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው።
“የኦሮሞ ህዝብ የመተሳሰብ፣ መከባበርና የመቻቻል ዘመን ተሻጋሪ ባህል ባለቤት በመሆኑ የጉጂ ህዝብ መቼም ቢሆን የዘራፊና የገዳይ ቡድን ተባባሪ አይሆንም” ብለዋል፡፡
በመድረኩ የተሳተፉ አባገዳዎች በንጹሀን ላይ ጥቃት በማድረስ ሀገር ለማፍረስ የተነሳውን ሽብርተኛ ቡድን ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ አንድ ሆኖ በመነሳት አሳልፎ እንዲሰጥ የመጨረሻ ትእዛዝ ሰጥተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!