Fana: At a Speed of Life!

በቂ የደም ክምችት አለኝ- የመተማ ደም ባንክ አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመተማ ደም ባንክ አገልግሎት በቂ የደም ክምችት እንዳለው ሀላፊው አቶ ወንድሙ አሰፋ አስታወቁ።
ተቋሙ በአለፈው ዓመት 2 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅዶ 2 ሺህ 141 ዩኒት ደም በመሰብሰብ ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል።
በ2014 ዓ.ም 3 ሺህ የኒት ደም ከበጎፈቃደኛ ደም ለገሾች ደም ለመሰብሰብ ደም ባንኩ ማቀዱን የገለፁት ሀላፊው፥ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 417 ዩኒት ደም ተሰብስቧል ነው ያሉት።
አሁን ላይ በቂ የሆነ የደም ክምችት ስላለ ሆስፒታሎች ስጋት አይገባቸውም የሚሉት አቶ ወንድሙ፥ አሁናዊው የህልውና ዘመቻው የደም ለጋሾችን ቁጥር በመጨመር ረገድ ጉልህ አበርክቶ አለው ብለዋል።
አሁን የተጀመረው ያለቅስቀሳ ደም የመለገስ የማህበረሰቡ ተሳትፎ በቀጣይም በተጠናከረ መንገድ መቀጠል እንዳለበት ደም ባንኩ ጥሪ አቅርቧል።
የመተማ እና አብርሃጅራ ሆስፒታሎች ከመተማ ደም ባንክ ደም በመቀበል የሚጠቀሙ ሆስፒታሎች ናቸው የሚሉት ሃላፊው፥ ከሌሎች በቅርበት ከሚገኙ ደም ባንኮች ጋርም ደም የመቀያየር ተግባሩ መቀጠሉን አስታውቀዋል።
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person, footwear and outdoors
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.