Fana: At a Speed of Life!

የወልቃይት ባለሃብቶችና አርሶ አደሮች የአካባቢያችንን ሰላም እየጠበቅን የግብርና ሥራችንን እናከናውናለን አሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካባቢያቸውን ሰላም አስተማማኝ አድርጎ ከመጠበቅ ጎን ለጎን የግብርና ሥራቸውን እያከናወኑ መሆኑን የወልቃይት ባለሃብቶችና አርሶ አደሮች ገለጹ።
የአካባቢውን ሰላም እና ደኅንነት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ጋር በመሆን በአስተማማኝ ሁኔታ እየጠበቁ መሆናቸውን በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በእርሻ ልማት የተሰማሩ ባለሃብቶችና አርሶአደሮች ገልጸዋል።
ባለሃብቶቹና አርሶአደሮቹ በዘንድሮው ዓመት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶችን ማምረታቸውን ለአሚኮ ተናግረዋል።
ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ማሽላና ማሾ በስፋት ማምረታቸውን የገለጹት አልሚዎቹ፥ አሸባሪው ትህነግ የአማራን ማንነትም ሆነ የአማራን ኢኮኖሚ ማዳከም እንደማይችል አስረድተዋል።
አሸባሪ ቡድኑ አካባቢውን በሃይል ተቆጣጥሮት በነበረበት ጊዜ አማራ እንዳያለማ ይሳደድና ያፈናቅል እንደነበር አስታውሰው፥ አሁን ላይ ግን ሁሉም ነገር ታሪክ ሆኗል ነው ያሉት።
በዘንድሮው ዓመት ተስማሚ የአየር ሁኔታና በቂ ዝናብ መኖሩ የዘሯቸው ሰብሎች በጥሩ ቁመና ላይ እንዲገኙና የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ ጠቅሰዋል።
አካባቢው ለሀገር የሚተርፍ ሃብት ባለቤት ነው ያሉት አልሚዎቹ የክልሉ መንግሥት እያደረገ ያለውን ክትትልና ድጋፍ በማጠናከር የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
በአረም ሥራ ላይ የተሰማሩ የጉልበት ሠራተኞች ከሥራቸው ጎን ለጎን የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት በአስተማማኝ አሁኔታ በመጠበቅ ረገድ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሠሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አወቀ መብራቱ እንደገለጹት፥ በዞኑ ሊለማ የሚችል ሰፊና ምቹ መሬት መኖሩን አስታውቀዋል።
አካባቢው ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን የሚያጎናጽፉ የእርሻ ልማት የሚከናወንበት ከመሆኑም ባለፈ፥ ልዩ ዝርያ ያላቸው የእንስሳት ሃብት ባለቤት መሆኑንም ተናግረዋል።
ወደፊት በዘርፎቹ የተሻለ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የግብርና ምርምር ማዕከላትን እና ሌሎች መሰል ተቋማትን መገንባት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.