Fana: At a Speed of Life!

የአለም ባንክ ለአዲስ አበባ ከተማ ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለም ባንክ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሲጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

አስተባባሪው÷ “ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር ጠቃሚ ውይይት አድርገናል፤ ባንኩ ከተማ አስተዳደሩ ለሚሰራቸው ልማቶች ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጦልናል” ብለዋል።

በውይይቱ ከተማሪዎች ምገባ ማዕከል ጋር በተያያዘ የመመገቢያ አደራሾችና ተጨማሪ መሰረተ ልማቶች በሚሰሩበት ዙሪያ መግባባት ላይ የተደረሰ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በከተማዋ የማገገሚያና የመልሶ ማቋቋም ማዕከል ለመገንባት መግባባት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሚጀመረው ሁለተኛ ዙር የከተማ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ልየታና በማጥራት ስራ ላይ ከስምምነትም መደረሱን ጠቅሰዋል።

ባለፈው በጀት ዓመት በአለም ባንክ ድጋፍ 128 የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ፣ 105 አዳራሾች ደግሞ በከተማ አስተዳደሩ መገንባቱን ገልጸው÷ አፈፃፀሙ የተሻለና የሚያበረታታ እንደሆነ እደንተገመገመ አስረድተዋል።

በ2014 በጀት አመት ለሚገነቡ መሰረተ ልማቶች የከተማ አስተዳደሩ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍቲኔት እንዲሁም የኮንስትራክሽን ልማት ቢሮዎች የንድፍ ስራ በፍጥነትና በጥራት እንዲያጠናቅቅ ግልፅ አቅጣጫ እንደተቀመጠ ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.