የኢሬቻ በዓል ሰላምንና የኮቪድ መከላከልን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በጅማ ከተማ ይከበራል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ ያለው የኢሬቻ በዓል ፍቅርና አንድነት የሚገለጽበት ህዝቡ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት በመሆኑ በበቂ ዝግጅት መከበር እንዳለበት የኦሮሚያ ክልል የሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሶሪ ዲንቃ ገለፁ።
የጅማ አካባቢ ህብረተሰብ በዓሉን በደመቀና የአካባቢን ሰላም በጠበቀ ሁኔታ እንደሚከበር የገለጹት ኃላፊው፥ ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ መልካምነትና ተፈጥሮዊ ውበት መሆኑን ለዓለም የሚያሳይበት እንደሆነም ተናግረዋል።
የጅማና የአካባቢው ህዝብ የቀደመ የሰላማዊነትና የመልካምንት እሴት ባለቤት እንደሆነ የገለጹት አቶ ሶሪ፥ የኢሬቻ በዓል የበለጠ መልካምነትን የሚያጎላ ነው ብለዋል።
ህብረተሰቡ ከከተማው የጸጥታ መዋቅር ጋር በመሆን በዓሉ በሰላም እንዲከበር በቅንጅት መሰራት እንደሚጠበቅበም አመልክተዋል።
በጅማ ከተማ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል ቅድመ ዝግጅት ላይ ባተኮረው ውይይት ላይ፥ እሬቻ በሚሊየን የሚቆጠር የኦሮሞ ህዝብ ወጥቶ የሚያከብረው ትልቅ በዓል መሆኑን አስረድተዋል።
ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ጽሁፍ ያቀረቡት አቶ ኤሊያስ ሸረፉ “ኢሬቻ ፈጣሪ የሚመሰገንበትና የኦሮሞ ህዝብ ባህላዊ ውበት ለዓለም የሚገለጽበት ነው” ብለዋል።
በዓሉ ጎብኚዎችን መሳብ እንዲችልና የቱሪዝም ዘርፉን አንዲያሳድግ ከዚህ የበለጠ ሊሰራበት እንደሚገባም በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።
በዓሉ በሰላምና ባህላዊ ውበቱን ጠብቆ እንዲከበር የሚመለከታቸው የጸጥታና የባልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤቶች ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውንም የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!